ዋትሳፕ ከጥቂት ቀናት በኋላ በተወሰኑ የስማርት ስልኮች ላይ አገልግሎቱን እንደሚያቋርጥ ገለጸ

 

የፌስቡክ እህት ኩባንያ የሆነው ዋትሳፕ (WhatsApp) በተወሰኑ ስማርት ስልኮች ላይ አገልግሎቱን ሊያቋርጥ እንደሆነ ገልጿል፡፡ አገልግሎቱን ከሚያቋርጥባቸው መካከልም የኖኪያ (Nokia Symbian S60)፣ ብላክቤሪ (BlackBerry OS እና Blackberry 10) እና ከዊንዶው ስልክ (Windows Phone 8.0) ሲሆኑ የኖኪያ (Nokia S40) ምርትም በማንኛውም ስዓት ሊቋረጥ ይችላል ተብሏል፡፡ የእነዚህ ስልክ ተጠቃሚ የሆኑ እና ቆየት ያሉ የሶፍትዌር እትሞችን (versions) የሚጠቀሙ አካላት በፈረንጆቹ ከታህሳስ 31/2017 ጀምሮ አገልግሎቱ እንደሚቋረጥ ተነግሯል፡፡ በመሆኑም ተጠቃሚዎች የዋትሳፕን አገልግሎት በቀጣይነት ለማግኘት ቴክኖሎጂያቸውን ማሻሻል እንደሚገባቸው እና የችግሩ ሰለባ የሆኑ የስልክ ተጠቃሚዎች የአንድሮይድ( Android)፣ የአይፎን( iPhone) እና የዊንዶው ስልክ ማሻሻያዎችን ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የጉግል፣ ሳምሰንግ፣ ኤችቲሲ (HTC) እና የዋንፕላስ (OnePlus) የስማርት ስልክ ተጠቃሚ የሆኑ እና የእትም (versions 2.3.7) ስልኮችም ከየካቲት 2020 ጀምሮ አገልግሎታቸው እንደሚቋረጥ ተነግሯል፡፡  

http://www.telegraph.co.uk/technology/2017/12/27/whatsapp-cease-working-older-smartphones-new-years-eve/