የአውሮፓ ሕብረት ኮሚሽን የቴክኖሎጂ ኩባንያዎችን አስጠነቀቀ

የአውሮፓ ሕብረት ኮሚሽን የተለያዩ የሶሻል ሚዲያ ኩባንያዎች ለብጥብጥ የሚጋብዙ አክራሪ ይዘት ያላቸውን ይዘቶች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የማያስተካክሉ ከሆነ የራሱን እርምጃ እንደሚወስድ ማስጠንቀቂያ ሰጠ፡፡  በአውሮፓ ሕብረት እያሻቀበ የመጣውን የሽብር መልክቶች ስርጭት በተመለከተ ኩባንያዎች ችግሩን በፍጥነት እንዲያስወግዱት በተደጋጋሚ ቢጠየቁም ተግባራዊ አለመደረጉን ኮሚሽኑ አውስቷል፡፡ ሆኖም እነዚህ ኩባንያዎች የራሳቸውን የማስፈጸሚያ መመሪያ አውጥተው በፍጥነት ጉዳዩን በማጤን ለስጋቱ እልባት የማይሰጡ ከሆነ የማያዳግም እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል፡፡ እንደ ኮሚሽኑ ገለጻ በሽብር መልዕክቶቹ ላይ ፈጣን የማስተካከያ ምላሽ የማይሰጥ ከሆነ ኩባንያዎችን እስከ ማገድ የሚደርስ ዕርምጃ ሊወስድ እንደሚችል ተናግሯል፡፡ የህብረቱ የደህንነት ኮሚሽነር ጁሊያን ኪንግ ለዘጋርዲያን እንደገለጹት ችግሩን ለመከላከል ለሁለት ዓመት ተጉዘናል ሆኖም እስካሁን ውጤት ባለመምጣቱ የመጨረሻው ውሳኔ ላይ ተደርሷል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ማስጠንቀቂያ የተሰጠቸው የኢንተርኔት ቴክኖሎጂ ኩባንያዎችም ፌስቡክ፣ ጎግል፣ ዩ ቲዩብ፣ ትዊተርና የመሳሰሉት መሆናቸውን ዘገባው አስታውሷል፡፡

እነዚህ ኩባንያዎች ቀደም ብሎ የጥላቻ ወሬዎችን አስመልክቶ ችግሩን እንዲያጤኑት በተጠየቁት መሰረት በተደጋጋሚ ቃል ቢገቡም እስካሁን ድረስ ያመጡት ውጤት እንደሌለ መረጃው ጨምሮ ገልጿል፡፡

https://www.theguardian.com/technology/2017/dec/07/eu-warns-tech-firms-facebook-google-youtube-twitter-remove-extremist-content-regulated-european-commission