የሳይበር ወንጀለኞች በባንክ ላይ አዲስ ጥቃት መክፈታቸው ተገለጸ

የሳይበር ወንጀለኞች አዲስ የማጭበርበሪያ ቴክኒክ በመጠቀም በባንክ ኤ.ቲ.ኤም ማሽን ላይ የተጠናከረ ጥቃት መክፈታቸው ተገለጸ፡፡ ሰሞኑን ኢሮፖል እና ትሬንድ ማይክሮ በጋራ ባወጡት ሪፖርት እንዳመለከቱት የሳይበር ወንጀለኞች በባንክ ኤ.ቲ.ኤም ማሽኖች ላይ ጥቃት ለመፈጸም በአካል መገኘት ሳይጠበቅባቸው በተቀነባበረ የኔትወርክ ጥቃት ብቻ ዘረፋ ማካሄድ መቻላቸው ተገልጿል፡፡ እንደዘገባው አዲሱ የጥቃት ዘመቻ የባንኩን ኔትወርክ በፊሽግ የኢ-ሜይል ጥቃት  (email phishing) በማውደም የደንበኞችን አካውንት በቀላሉ መቆጣጠርና ገንዘብ መዝረፍ መቻላቸውን ገልጿል፡፡ እስካሁን በጥቃቱ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ የሰረቁ ሲሆን ሁኔታው በዚሁ ከቀጠለ ሁሉም የባንክ እንቅስቃሴ በወንጀለኞች ቁጥጥር ስር ይሆናል የሚል ስጋት እንዳለ ሪፖርቱ ገልጿል፡፡ አጥቂዎች በየጊዜው የሚጠቀሙት ያልተለመደ ማልዌር ስጋቱን ለመከላከል አስቸጋሪ እንዳደረገውና የኢንዱስትሪውን እንቅስቃሴም አደጋ ላይ ሊጥለው እንደሚችል ተዘግቧል፡፡ ይህን ተከትሎም በዘርፉ ላይ ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊደረግበት እንደሚገባ በሪፖርቱ ተብራርቷል፡፡      

http://www.ibtimes.co.uk/global-banks-alert-hackers-launch-covert-atm-heists-via-malware-1641030