ተቋማት የሳይበር ጥቃትን ቀድመው መመከት እንዳለባቸው ተጠቆመ

አይ.ቲ ኒውስ አፍሪካ (itnewsafrica.com) እንደዘገበው የቴክኖሎጂ ኩባንያው Cisco ባወጣው የ2017 ግማሽ አመት የሳይበር ደህንት ሪፖርት መሰረት በዓለም ከሚደረጉ የዲጂታል ንግድ እንቅስቃሴዎች መካከል 49 በመቶ የሚሆኑት የንግድ እንቅስቃሴዎች በ2016 ብቻ ቢያንስ አንድ ጊዜ የሳይበር ጥቃት እንደደረሰባቸው ገልጿል፡፡ ከዚህም ውስጥ 39 በመቶው የራንሰምዌር ጥቃት (ransomware) እንደሆነ አስታውቋል፡፡ የሳይበር ጥቃት ከጊዜ ጊዜ እየጨመረ መሄዱን የሚጠቅሰው መረጃው በሀገረ አሜሪካ ብቻ  በፈረንጆቹ 2015 በአገሪቱ የተከሰተው የሳይበር ጥቃት በ2016 ወደ 300 በመቶ ማደጉን አውስቷል፡፡ ችግሩን ለመቀነስ ጠንከር ያለ የደህንነት ጥበቃና የስጋት ምርምር በማድረግ ጉዳቱ ከመከሰቱ አስቀድሞ ጉዳዩን መለየትና ጥቃቱን ማክሸፍ ያስፈልጋል ሲል ዘገባው ጠቅሷል፡፡  

ዘገባው ጨምሮ እንደጠቆመው የቢዝነስ ተቋማት እራሳቸውን ከሳይበር ጥቃት ለመከላከል፤ ጥቃቱ ከመከሰቱ በፊት አስቀድመው መተንበይና በቂ መረጃ ማሰባሰብ፣ የመከላከያ ቴክኖሎጂዎችን ማጠናከር፣ አፋጣኝ ግብረ መልስ መስጠትና የመሳሰሉትን ማድረግ እንደሚገባቸው ጠቁሟል፡፡

http://www.itnewsafrica.com/2017/09/organisations-must-disrupt-cyber-attacks-before-they-become-a-business-disrupt/