የሳይበር ደሕንነት በሥርዓተ-ትምህርት ውስጥ እንዲካተት ተጠየቀ

በዓለም እየተስፋፋ የመጣውን የሳይበር ወንጀል ለመቋቋም በደቡብ አፍሪካ የረጅምና የአጭር ጊዜ የአይ.ሲ.ቲ ክህሎት ስልጠና ያስፈልጋል ሲል በአገሪቱ የሚገኘው Joburg Centre for Software Engineering's (JCSE) አስታወቀ፡፡ ድርጅቱ በ7ኛው የአይ.ሲ.ቲ ዓመታዊ የክህሎት ቅኝቱ እንዳረጋገጠው ደቡብ አፍሪካ በአህጉሪቱ ከሚገኙ እንደ ኬንያ፣ ናይጄሪያና ግብጽ ከመሳሰሉ አገራት ጋር ስትወዳደር በአይ.ሲ.ቲ መስክ የሚጠበቅባትን እየሰራች አይደለም ሲል ተችቷል፡፡ በመሆኑም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን ስጋት ለመቀነስ የሳይበር ክህሎትን ማሳደግ  አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው ሲል ጠቁሟል፡፡ እንደ አይ.ቲ ኒውስ አፍሪካ (itnews africa) ዘገባ በተለይ የኢንዱስትሪ ተቋማት ይህን ተግባራዊ የማያደርጉ ከሆነ ከትርፍ ይልቅ የሚያጋጥማቸው ኪሳራ እየገዘፈ ይሄዳል ሲል አስጠንቅቋል፡፡ ችግሩን ለማቃለልም የሳይበር ደሕንነትን በትምህርት ቤቶች፣ በኮሌጆችና በዩኒቨርስቲዎች በሥርዓተ ትምሕርት እንዲካተትና በሌላ በኩል በኢንተርንሽፕ፣ በኦንላይን ስልጠናና በመሳሰሉት ደግሞ የዜጎችን ክህሎትን መገንባት ያስፈልጋል ሲል አሳስቧል፡፡

JCSE ይህን ያስነበበው የሳይበር ደሕንነት ክህሎት ዝቅተኛ በሆነባቸው አገራት በግልና በመንግስት ተቋማት ላይ ተደጋግሞ የደረሰውን ጥቃት በማስታወስ ነው፡፡

http://www.itnewsafrica.com/2017/08/cybercrime-growth-highlights-need-for-short-and-long-term-ict-education-plans-in-south-africa/