“የሃሳብ ድህነትን ታግሎ ያሸነፈ መሪ”

የታላቁ መሪ መለስ ዜናዊ 5ተኛ አመት መታሰቢያ "የሃሳብ ድህነትን ታግሎ ያሸነፈ መሪ" በሚል መሪ ቃል ነሃሴ 15 ቀን 2009 ዓ/ም በኢንፎርሜሽን  መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢመደኤ) ታስቦ ዋለ፡፡ ዕለቱ በህሊና ጸሎት እና በጧፍ ማብራት ፕሮግራም ታስቦ ውሏል፡፡

የታላቁ መሪ መለስ ዜናዊ 5ተኛ አመት መታሰቢያ በተቋም ደረጃ ሲታሰብ በዋናነት ከታላቁ መሪ መለስ ዜናዊ የትግል ህይወት፣ የአመራር ክህሎት፣ ከስብእናቸው እንዲሁም ከአስተሳሰባቸው በመማር እና ለሃገራቸው ያበረከቱትን አስተዋጽኦ በመዘከር እንዲሁም ሌጋሲያቸውን ለማስቀጠልና የተሻለች ኢትዮጵያን ለመገንባት ትልቅ አቅም የሚፈጥር እንደሆነ በእለቱ ተገልጿል፡፡

ክቡር ሜ/ጄኔራል ተክለብርሃን ወ/አረጋይ፡ የኢመደኤ ዋና ዳይሬክተር በዕለቱ ተገኝተው ባስተላለፉት መልእክት የታላቁን መሪ መለስ ዜናዊ ህይወት ከሌላው ኢትዮጵያዊ ህይወት ነጥሎ መመልከት እንደማይቻል ገልጸው፤ በመላው ኢትዮጵያውያን ልብ ውስጥ የታላቁ መሪ መለስ ዜናዊ አስተሳሰብና እምነት እንዳለ ሁሉ በታላቁ መሪ መለስ ዜናዊ አስተሳሰብና እምነት ውስጥም የህዝቦች ጥቅምና ፍላጎት ይንጸባረቅ እንደነበር ገልጸዋል፡፡ በመሆኑም የታላቁ መሪ መለስ ዜናዊ መታሰቢያ በየአመቱ ስናስብ ከታላቁ መሪ ፖለቲካዊ ስብዕናቸውና ማንነታቸው መገለጫ ባህሪያትን በመውረስና በመላበስ ጭምር እንደሆነ ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡