ብሔራዊ የሳይበር መከላከል የልዩ ታለንት ውድድር

በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ የሳይበር ታለንት ልማት ፕሮግራም በሀገር አቀፍ ደረጃ የብሄራዊ የሳይበር መከላከል የልዩ ታለንት ውድድር አዘጋጅቷል፡፡ በመሆኑም በውድድሩ ላይ ለመካፈል ከዚህ በፊት የተመዘገባችሁ ከሐምሌ 2009 ዓ.ም መጨረሻ ጀምሮ ማጣራቱ እና ውድድሩ መከናወን ስለሚጀምር እንድትዘጋጁ፤ እንዲሁም ያልተመዘገባችሁ ባሉት ጥቂት ቀናት ውስጥ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ለተጨማሪ መረጃ እንዲሁም ለመመዝገብ፡ በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋናው መስሪያ ቤት (ብስራተ ገብርኤል አዶት ህንጻ አጠገብ አፍሪካ ኢንሹራንስ ህንጻ) በአካል በመምጣት መመዝገብ የምትችሉ ሲሆን፤ በተጨማሪም የመመዝገቢያ ፎርሙን ከዌብሳይት ወይም ከፌስቡክ ገጻችን ወስዳችሁ በመሙላት እና በ cybertalentethiopia@insa.gov.et ላይ በመላክ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ ለተጨማሪ መረጃ፡-  

    https://www.facebook.com/INSA.ETHIOPIA/