የሳይበር ደህንነት ስጋት ማሳሰቢያ

"Decrypt Wannacry" የተሰኘ የሳይበር ጥቃት በአገራት የሳይበር መሰረተ-ልማት ላይ ከፍተኛ የደህንነት ስጋት እያስከተለ እንደሆነ ተገለጸ  

 

ከግንቦት 4 ቀን 2009 ዓ/ም ጀምሮ ኢትዮጵያን ጨምሮ በ150 ሀገራት የተከሰተውና "Decrypt Wannacry" ወይም "WANNA CRY MALWARE"    በመባል የሚጠራው የሳይበር ጥቃት  በአገራት የሳይበር መሰረተ-ልማት ላይ ከፍተኛ የደህንነት ስጋት አስከትሏል፡፡ በመሆኑም በኢትዮጵያ ውስጥ ጥቃቱ ዒላማ አድርጎባቸዋል  ተብለው ከተለዩ ተቋማት መካከል፡-

  1. የቴሌኮሙዩኒኬሽን መሠረተ-ልማት፤
  2. የገንዘብ እና የፋይናንስ መሠረተ-ልማት፤
  3. የኤሌክትሪክ እና የኢንዳስትሪ መቆጣጠሪያ ሥርዓቶች፤ እንዲሁም
  4. ኤም አር አይ (MRI) ባለቤት የሆኑ ሆስፒታሎች ዋንኞቹ ናቸው፡፡
የደህንነት ስጋቱ (vulnerabilities) የሚስፋፋውም የዊንዶስ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ክፍተት (Window Operating System SMP vulnerabilities) አማካኝነት መሆኑ ተደርሶበታል፡፡  በመሆኑም ከላይ የተጠቀሱትን ተቋማት ጨምሮ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የሳይበር መሰረተ-ልማት ባለቤቶች በተለይም የዊንዶስ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ተጠቃሚ የሆኑ ተቋማት የጥቃቱ ሰለባ እንዳይሆኑ የዊንዶውስ ኦፕሬቲንግ ሲስተም የደህንነት ክፍተት መድፈንና ማሻሻል (Update) ማድረግ   እንደሚገባቸው እናሳውቃለን፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ ለሚነሱ ማንኛውም ዓይነት የሳይበር ደህንነት ስጋት  በኤጀንሲው ነፃ የስልክ መስመር 933 በመደወል ወይም ethiocert.insa.gov.et ላይ መልዕክት በመላክ አስፈላጊውን ድጋፍ መጠየቅ እንደሚቻል የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ መልዕክት ያስተላልፋል፡፡