ቻይና በሞባይል ስልኮች አማካኝነት የመታወቂያ ካርድ አገልግሎት በ2018 ልትጀምር ነው

 

አብዛኛዎቻችን የመታወቂያ ካርዳችንን ረስተን ከቤት ልንወጣ እንችላለን፡፡ ይህን ችግር ይቀርፋል ያለችውን ቴክኖሎጂም ቻይና ተግባራዊ ማድረግ ለመጀመር ማሰቧን ገልጻለች፡፡ በቻይና የጉዋንዡ ግዛት የሙከራ ፕሮግራሙ መጀመሩን እና ይህ ሙከራም በቀጣይ በሃገሪቱ የቀድሞውን የመታወቂያ ካርድ ስለሚተካ ተለምዷዊውን መታወቂያ ካድ በኪሳቸው ይዘው መጓዝ ያበቃለታል ተብሏል፡፡ ከ10 በላይ የቴክኖሎጂ ተቋማት ድጋፍ የተደረገለት አዲሱ መታወቂያ ዘመቻ በሃገር አቀፍ ደረጃ በሚቀጥለው ጥር/2018 ጀምሮ ወደ ትግበራ እንደሚገባ ተጠቅሷል፡፡ መታወቂያዎቹ በሁለት መልኩ የሚቀርቡ ሲሆን በዊቻት (WeChat) ላይ በሚጫን አነስተኛ መተግበሪያ እንዲሁም በህዝብ ደህንነት ቢሮ ይበልጥ ደህንነቱ የተጠበቀ ፈጣን ምላሽ (Quick Response (QR) ኮድ ፍተሻን ያካተተ መሆኑ ታውቋል፡፡ ለመታወቂያው መሠረታዊ ለሆኑ መረጃዎች ብቻ የፊት ገጽ ስካን (scan) እንደሚያስፈልገው ታውቋል፡፡ ምን አልባት የግለሰቡ ስልክ ከጠፋ ተጠቃሚው ባለ ስምንት አኃዝ የግል መለያ ቁጥሩን (PIN) እንደገና በማዘጋጀት የመታወቂያው አገልግሎት እንዲቋረጥ ማድረግ ይችላሉ ተብሏል፡፡

https://news.cgtn.com/news/30676a4d34637a6333566d54/share_p.html