ኔቶ በሳይበር ጥቃት ላይ የሚወሰደው አጸፋዊ እርምጃ ጠንካራ ሊሆን ይገባል ሲል አሳሰበ

የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃልኪዳን ድርጅት (NATO) አባል ሃገራት በመንግስት ድጋፍ የሚፈጸሙ የኮምፒውተር ጥቃቶች ላይ የሚወሰደው እርምጃ ጠንካራ መሆን ይገባዋል ሲሉ አሳሰቡ፡፡ በዚህም የጦር ቃልኪዳኑ አባላት በጥቃት አድራሾች ላይ የሳይበር ጥቃቶችን በመፈጸም የጠላትን ኔትዎርክ ከጥቅም ውጪ ማድረግ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ አሜሪካ ከ2011 ጀምሮ ድረ-ገጾችን ማገድ እና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂን ማጥፋት የሚያስችል የሳይበር ጦር መሳሪያ አልያም ኮምፒውተር ኮድ ተግብራለች ያለው መረጃው ጥቂት የማይባሉ የኔቶ አባል ሃገራት ከአየር ጥቃቶች ይልቅ በጠላት የሃይል ተቋማት ላይ የሳይበር ጥቃት ማድረስን እንደሚፈልጉም ተነግሯል፡፡ በአለም አቀፍ ደረጃ በ2017 ከመቼውም ጊዜ በላይ በርከት ባሉ ግዙፍ ኩባንያዎች፣ ወደቦችና የህዝብ አገልግሎት መስጫዎች ላይ ያልተጠበቁ የሳይበር ጥቃቶች ተፈጽመዋል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

https://www.reuters.com/article/us-nato-cyber/nato-mulls-offensive-defense-with-cyber-warfare-rules-idUSKBN1DU1G4